About us

🏛️

የፕሬዚደንት መልዕክት

OFFICIAL
Court President
ዋሲሁን ከበደ ምቦ

የፍርድ ቤቱ ፕሬዚደንት

Court President

🌟 እንኳን ወደ አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፍርድ ቤት ድረገጽ እና ጉዳዮች ፍሰት አስተዳደር ሲስተም በደህና መጡ!

የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፍርድ ቤት ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ለተገልጋይ ማህበረሰብ ቀልጣፋ፣ ተገማች እና ታአማኒነት ያለውን አገልግሎት ለመስጠት እየታተረ መቆየቱ ይታወቃል።

የፍርድ ቤታችን አገልግሎት አሰጣጥ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የመጣ ቢሆንም አሁን ላይ ፍርድ ቤቶች አገልግሎታቸውን በቴክኖሎጂ በታገዘ መልክ እንዲሰጡ ወቅቱ ያስገድዳል።

📌 ፍርድ ቤቶች ቀልጣፋ፣ ተገማች፣ ወጪ ቆጣቢ፣ ተደራሽ እና ታአማንነት ያለውን አገልግሎት እንዲሰጡ ያስችላቸው ዘንድ ተቋማቸውን ዲጂታላይዝ ማድረግ የግድ ይላል።

አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፍርድ ቤትም አገልግሎቱን ለማሳለጥ የተለያዩ ማሻሻያዎችን እያደረገ ቆይቷል። ከእነዚህም መካከል አንዱ ድረገጽ ይፋ መደረጉ እና ቪዲዮ ኮንፈረንስ ችሎት ሥርዓት መዘርጋቱ ነው።

በድረገጻችን የሚያሳልፉት ቆይታ መልካም እንዲሆን ከወዲሁ እመኛለሁ!

— የፍርድ ቤቱ ፕሬዚደንት
⚖️ ፍትህ ለሁሉም 🏛️ አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፍርድ ቤት 📅 2026 ዓ.ም