የፍ/ሔር መረጃ
🏛️
የፍትሐብሔር ክርክር
የተለመዱ የፍትሐብሔር ክርክር ዓይነቶች
📂
የክርክር ዓይነቶች
🏠 የኪራይ ክርክር
📜 የውል ጥሰት
💰 የዕዳ ክስ
🏡 የቤት ውርስ ክርክር
📦 የንብረት ይዞታ ክርክር
👨👩👧 የቤተሰብ ጉዳይ
📋
የፍትሐብሔር ይግባኝ ለማቅረብ መሟላት ያለባቸው ነገሮች
- 1 የተከራካሪ ወገኖች ስም እና አድራሻ።
- 2 የክሱ ምክንያት በግልጽ መገለጽ እለበት።
- 3 ዋና ወይም ኦርጅናል የሰነድ ማስረጃ ለማገናዘብ መቅረብ አለበት።
- 4 የክርክሩ ገንዘብ መጠን በእቤቱታው ላይ በግልጽ ተጽፎ መቅረብ አለበት።
- 5 የማስረጃ ዝርዝር የያዘ መሆን አለበት፤ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ አንቀጽ 145 መሰረት መቅረብ ያለበት ማስረጃ ካለ ተጠቅሶ መቅረብ አለበት።
- 6 ከሳሽ የሚያመለክተው በራሱ ከሆነ እቤቱታው ላይ በሁሉም ገጾች መፈረም ይኖርበታል።
- 7 ማስረጃዎች የሚያስረዱት ጭብጥ ተገልጾ መቅረብ አለበት።
- 8 ከሳሽ የሚያመለክተው በጠበቃ በኩል ከሆነ አቤቱታው በቲተር መፈረም ይኖርበታል፤ የጥብቅና አገልግሎት ውል ጠበቃው እና ባለጉዳይ /ደንበኛ/የተፈራረሙበት መቅረብ ይኖርበታል።
- 9 የጥብቅና አገልግሎት ውል ላይ በነፃ ለማገልገል ተስማምቻለሁ የሚል ከሆነ ከፍትህ መምሪያ/ቢሮ/ የተፃፈ ደብዳቤ አብሮ መያያዝ እለበት።
- 10 ከሳሽ ታራሚ ከሆነ በማመልከቻው ላይ በሁሉም ገጾች መፈረም እና በማረሚያ ቤቱ ማህተም መረጋገጥ አለበት።
- 11 የሚቀርበው የክስ አቤቱታ ግልጽና አጭር መሆን አለበት፤ አቤቱታው ከሶስት ገጽ ያልበለጠ መሆን ይኖርበታል፤ ሆኖም ግን በልዩ ሁኔታ እንደ ጉዳይ አይነት ታይቶ ልመራ ይችላል።
📌
መዝገብ እንዲንቀሳቀስ የሚቀርብ አቤቱታ
- 1 አቤቱታ የሚቀርብበት ችሎት ስም፣
- 2 የተከራካሪ ወገኖች ስም እና አድራሻ፣
- 3 መዝገቡ የተዘጋበት ቀን፣ መዝገብ ቁጥር፣ በመዝጋቱ ምክንያት ያጡትን መብት እና እንዲንቀሳቅሰ የተጠየቀበት/ህጋዊ /ምክንያት በእቤቱታው ላይ ተገልጾ እና ተፈርሞ መቅረብ ይኖርበታል።
📄
የውሳኔ/ትዕዛዝ/ብይን ግልባጭ ለመውሰድ መሟላት ያለባቸው ነገሮች
1
ባለጉዳይ ከሆነ መታወቂያ ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
2
ተወካይ ከሆነ ህጋዊ ውኪልና ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
3
ሞግዝት ከሆነ በፍ/ቤት የተሰጠ የሞግዝትነት ውሳኔ ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
⚖️
መብቶች እና ግዴታዎች
✅ ክስ የማቅረብ መብት
✅ ማስረጃ የማቅረብ መብት
✅ በጠበቃ የመታገዝ መብት
✅ የፍርድ ቤት ሂደትን የመከታተል መብት
✅ ይግባኝ የማቅረብ መብት
🛡️ በህግ ክልል ውስጥ የመቆየት ግዴታ
🛡️ የፍርድ ቤት ትእዛዝ የማክበር ግዴታ
🛡️ እውነቱን የመናገር ግዴታ
መረጃው በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ መሰረት የተዘጋጀ ነው