የአርባ ምንጭ ወረዳ ፍርድ ቤት ተልዕኮ፣ ራዕይ እና መሰረታዊ እሴቶች
ከማናቸውም ተጽዕኖ ነጻ በመሆን ሕግን በመተርጎም ክርክሮች ላይ እልባት በመስጠት በሕገ መንግስቱና በህግ ብቻ የሚመራ የዳኝነት አካል በመፍጠር በገለልተኛነት፣ በሕግ አገልጋይነት ስሜት፣ በቅልጥፍና በሚዛናዊነት ለህብረተሰቡ ጥራት ያለውን የዳኝነት አገልግሎት በመስጠት የሕግ የበላይነትን ማረጋገጥ ነው።
በ2022 ዓ.ም የአርባ ምንጭ ወረዳ ፍርድ ቤት ገለልተኛና ነጻ በመሆን ተደራሽነት ያለውን ፍትህ በተፋጠነ ሁኔታ እና ጥራት ያለውን አገልግሎት በመስጠት እርካታና አመኔታ ያተረፈ ፍርድ ቤት ሆኖ ማየት ነው።