የወንጀል መረጃ
⚖️
የወንጀል ጉዳይ መረጃ
አስፈላጊ መስፈርቶች እና መብቶች
📋
የወንጀል አቤቱታ ለማቅረብ መሟላት ያለባቸው ነገሮች
- 1 አቤቱታ አቅራቢው ዓ/ህግ ከሆነ በታወቀ እና ዘርፉ ፊርማ እና የታሸገ ማኅተም ያስፈልገዋል።
- 2 አቤቱታ አቅራቢው ታራሚ ከሆነ የሚገኝበት ማረሚያ ቤት ስም እንዲሁም በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ማኅተም እና የይግባኝ ባዮች ፊርማ ሊኖር ይገባል።
- 3 ታራሚ ከሆነ የሚገኝበት ማረሚያ ቤት ስም እንዲሁም በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ማህተም እና የይግባኝ ባዮች ፊርማ ሊኖረው ይገባል።
- 4 የስር ፍ/ቤቶች የመዝገብ ግልባጭ በመሸኛ ተደግፎና በፍ/ቤቱ ማህተም የችሎት እና ልዩ ልዩ አባሪዎች ተረጋግጦ መቅረብ ይኖርበታል።
- 5 የስር ፍ/ቤት መዝገብ ቀን፣ ፋይል ቁጥር፣ የተሰየመ ዳኛ ስም እና ተከራካሪ ወገኖች ስም እና የችሎት ስራ በሚታይ መልኩ ኮፒ ሆኖ መቅረብ እለበት።
- 6 በአቤቱታ ላይ የይግባኝ ባዮች/መልስ ሰጪዎች ስም፣ የመኖሪያ አድራሻ እና ቀን እንዲሁም የስር ፍ/ቤት ስም፣ የመዝገብ ቁጥር እና ውሳኔ የተሰጠበት ቀን በግልጽ መጻፍ አለበት።
- 7 ለይግባኝ ምክንያት የሆኑ ቅሬታ ነጥቦችን መግለጽ አለበት፤ እንዲሁም በይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት እንዲታረም የሚፈልጉት ነገር እና የሚጠይቁትን ዳኝነት መግለጽ አለባቸው።
- 8 ጊዜው ያለፈበት ከሆነ እና ማስፈቀጃው ቀርቦበት የተፈቀደ ከሆነ ይኸው ተገልጸ መ/ቁጥር ተጽፎ መቅረብ አለበት።
- 9 አቤቱታው የቀረበው በአንድ(1) መላሽ ላይ ከሆነ በሁለት(2) ቅጂ ይቀርባል፤ ከመላሽ በላይ ከሆነ ቅጂው በአንድ እየጨመረ ስለሚሄድ በዚህ መሰረት ተዘጋጅቶ መቅረብ ይኖርበታል።
- 10 በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ መሰረት እንደ አግባብነቱ የሚያስፈልጉ ነገሮች ተሟልተው መቅረብ አለባቸው።
⚖️
የተከሳሹ መብቶች
🤐
ዝምታ የመቆየት መብት
🧑⚖️
ጠበቃ የማግኘት መብት
🏛️
በፍርድ ቤት ቀርቦ የመሰማት መብት
📄
ማስረጃ የማቅረብ መብት
👥
ምስክሮችን የመጠየቅ መብት
📬
ይግባኝ የማቅረብ መብት
⚖️
ፍትሃዊ የፍርድ ሂደት የማግኘት መብት
🛡️
የማይገባ ቅጣት እንዳይጣልበት የመጠበቅ መብት
መረጃው በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ-ሥርዓት ሕግ መሰረት የተዘጋጀ ነው