የፍ/ሔር መረጃ

🏛️

የፍትሐብሔር ክርክር

የተለመዱ የፍትሐብሔር ክርክር ዓይነቶች

📂

የክርክር ዓይነቶች

🏠 የኪራይ ክርክር 📜 የውል ጥሰት 💰 የዕዳ ክስ 🏡 የቤት ውርስ ክርክር 📦 የንብረት ይዞታ ክርክር 👨‍👩‍👧 የቤተሰብ ጉዳይ
📋

የፍትሐብሔር ይግባኝ ለማቅረብ መሟላት ያለባቸው ነገሮች

  1. 1 የተከራካሪ ወገኖች ስም እና አድራሻ።
  2. 2 የክሱ ምክንያት በግልጽ መገለጽ እለበት።
  3. 3 ዋና ወይም ኦርጅናል የሰነድ ማስረጃ ለማገናዘብ መቅረብ አለበት።
  4. 4 የክርክሩ ገንዘብ መጠን በእቤቱታው ላይ በግልጽ ተጽፎ መቅረብ አለበት።
  5. 5 የማስረጃ ዝርዝር የያዘ መሆን አለበት፤ በፍ/ሥ/ሥ/ህግ አንቀጽ 145 መሰረት መቅረብ ያለበት ማስረጃ ካለ ተጠቅሶ መቅረብ አለበት።
  6. 6 ከሳሽ የሚያመለክተው በራሱ ከሆነ እቤቱታው ላይ በሁሉም ገጾች መፈረም ይኖርበታል።
  7. 7 ማስረጃዎች የሚያስረዱት ጭብጥ ተገልጾ መቅረብ አለበት።
  8. 8 ከሳሽ የሚያመለክተው በጠበቃ በኩል ከሆነ አቤቱታው በቲተር መፈረም ይኖርበታል፤ የጥብቅና አገልግሎት ውል ጠበቃው እና ባለጉዳይ /ደንበኛ/የተፈራረሙበት መቅረብ ይኖርበታል።
  9. 9 የጥብቅና አገልግሎት ውል ላይ በነፃ ለማገልገል ተስማምቻለሁ የሚል ከሆነ ከፍትህ መምሪያ/ቢሮ/ የተፃፈ ደብዳቤ አብሮ መያያዝ እለበት።
  10. 10 ከሳሽ ታራሚ ከሆነ በማመልከቻው ላይ በሁሉም ገጾች መፈረም እና በማረሚያ ቤቱ ማህተም መረጋገጥ አለበት።
  11. 11 የሚቀርበው የክስ አቤቱታ ግልጽና አጭር መሆን አለበት፤ አቤቱታው ከሶስት ገጽ ያልበለጠ መሆን ይኖርበታል፤ ሆኖም ግን በልዩ ሁኔታ እንደ ጉዳይ አይነት ታይቶ ልመራ ይችላል።
📌

መዝገብ እንዲንቀሳቀስ የሚቀርብ አቤቱታ

  • 1 አቤቱታ የሚቀርብበት ችሎት ስም፣
  • 2 የተከራካሪ ወገኖች ስም እና አድራሻ፣
  • 3 መዝገቡ የተዘጋበት ቀን፣ መዝገብ ቁጥር፣ በመዝጋቱ ምክንያት ያጡትን መብት እና እንዲንቀሳቅሰ የተጠየቀበት/ህጋዊ /ምክንያት በእቤቱታው ላይ ተገልጾ እና ተፈርሞ መቅረብ ይኖርበታል።
📄

የውሳኔ/ትዕዛዝ/ብይን ግልባጭ ለመውሰድ መሟላት ያለባቸው ነገሮች

1

ባለጉዳይ ከሆነ መታወቂያ ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።

2

ተወካይ ከሆነ ህጋዊ ውኪልና ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።

3

ሞግዝት ከሆነ በፍ/ቤት የተሰጠ የሞግዝትነት ውሳኔ ይዘው መቅረብ ይጠበቅባቸዋል።

⚖️

መብቶች እና ግዴታዎች

✅ ክስ የማቅረብ መብት
✅ ማስረጃ የማቅረብ መብት
✅ በጠበቃ የመታገዝ መብት
✅ የፍርድ ቤት ሂደትን የመከታተል መብት
✅ ይግባኝ የማቅረብ መብት
🛡️ በህግ ክልል ውስጥ የመቆየት ግዴታ
🛡️ የፍርድ ቤት ትእዛዝ የማክበር ግዴታ
🛡️ እውነቱን የመናገር ግዴታ
መረጃው በፍትሐብሔር ሥነ-ሥርዓት ሕግ መሰረት የተዘጋጀ ነው