የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት የሴቶችና ህፃናት ልዩ ችሎት በ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የሥራ ሪፖርት ግምገማ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ።
አርባ ምንጭ ፦ሰኔ 30/2018 ዓ.ም (አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት)፦
በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፍ/ቤት የሴቶችና ህፃናት ልዩ ችሎት በ2018 በጀት ዓመት ማጠቃለያ የሥራ ሪፖርት ግምገማ እና የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ከቀበሌ ከመጡ ሰቶች ህፃናት ተወካዮች እና ከተለያዩ ባለድርሻ ሴክተር አካላት ጋር ተካሂዷል።
የሴቶችና ህፃናት ልዩ ችሎት በሴቶች እና ህፃናት ላይ የሚደርሱ ፆታዊ፣ አካላዊ እንዲሁም ሥነ_ልቦናዊ ጥቃቶችን ለመከላከል ብሎም ፈጣንና ሚዛናዊ የፍትህ አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመ መሆኑን አቶ ዋሲሁን ከበደ የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፍርድ ቤት ፕረዚዳንት በመድረኩ ባስተላለፉት መልዕክት አብራርተዋል።
የመድረኩ ዓላማው በፍትህ ስርዓቱ ውስጥ የሚያልፉ እና የሚገለጌሉ ሴቶችና ህፃናት ሳይጉላሉ ተገቢውን ፈጣንና ጥራት ያለውን ፍትህ እንዲያገኙ ማድረግ መሆኑን አቶ ዋሲሁን አክለው ገልፀዋል።
በመድረኩም ሰፊ ጥያቄ እና አስተያየት ተነስቶ ውይይት ተደርጎበታል ።


