አርባ ምንጭ፦ሐምሌ 2/2018 ዓ/ም (የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ መንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት)
የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የዳኝነትና የፍትህ አካላት የጋራ ጥምረት የ2018 ዓ/ም የአገልግሎት አሰጣጥ እና ቅንጅታዊ አሰራርን በተመለከተ ግምገማ አካሂደዋል።
የአርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የዳኝነትና ፍትህ ስርአቱን ውጤታማ ለማድረግ እየተካሄደ የሚገኘው ቅንጅታዊ አሰራር በማጠናከር በዘርፉ የላቀ ስኬት ማስመዝገብ መቻል እንዳለበት በመድረኩ ተገልጿል።
መድረኩ የተቋማቱን ነፃነት በጠበቀ መልኩ የሚመክሩበት፣ መልካም ተሞክሮዎችን የሚለዋወጡበት እና ቀልጣፋ፣ ጥራት ያለውና ፍትሀዊ አገልግሎት ለህብረተሰቡ ለመስጠት የሚያስችል የጋራ አቅጣጫ የተቀመጠበት መሆኑ ተመላክቷል።
የዓመቱ አፈፃፀም በጥንካሬና በድክመት በዝርዝር የተገመገመ ሲሆን፣ በቀጣይም የህግ የበላይነትን ይበልጥ ለማረጋገጥ ስራዎችን አጠናክሮ ማስኬድ እንደሚገባ በተሳታፊዎች አፅንኦት ተሰጥቶበታል።
በዓመቱ በአራቱ ተቋማት ማለትም በፍርድ ቤት፣በፍትህ ጽ/ቤት፣ በፖሊስ እና ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት የተሰሩ ሥራዎች በጥልቀት ተገምግሞ የጋራ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን ውይይቱን አቶ ዋሲሁን ከበደ የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፍርድ ቤት መርተዋል።


