አርባ ምንጭ ፦ መጋቢት 3/2018 ዓ.ም (አርባ ምንጭ ዙሪያ ወረዳ የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት)፦558 የክላሽ ኢንኮቭ ጠመንጃ ጥይት በተሽከርካሪ ደብቆ ከኮንሶ ወደ አርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ዘይሴ ቀበሌ ይዞ ሊገባ የሞከረው ተከሳሽ ኮሴ ኤርካዶ በ8 ዓመት ጽኑ እስራትና 10ሺ ብር የገንዘብ ቅጣት ተላልፎበታል።
ተከሳሹ በአከባቢው ለሚንቀሳቀሱ ህገ-ወጥ ቡድኖች ለማድረስ አስቦ ቢንቀሳቀስም በአከባቢው ለጸጥታ ስራ በተሠማሩ ፖሊሶች ድንገተኛ ፍተሻ በቁጥጥር ስር መዋሉን መዘገባችን ይታወሳል።
የዚህ የወንጀል ድርጊት ፈጻሚ ላይ ፖሊስ ያጣራውን ምርመራ በሰው ምስክርና በኤግዚቢትነት አስደግፎ ለሚመለከተው አካል ልኳል መዝገቡ የደረሰውም ዐቃቤ-ህግ በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ፍርድ ቤት ክስ መስርቶ ሲታይ ከቆየ በኋላ መጋቢት 03/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት ተከሳሹን ጥፋተኛ በማለት በ8 አመት ፅኑ እስራትና 10 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት አስተላልፎበታል።
